ሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት | EOTC N. CaNvAz Diocese

በሀገረ ስብከቱ ሥር ባሉ አድባራትና ገዳማት የተከናወኑ ፕሮጀክቶች
በሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት የሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ካቴድራል በላስ ቬጋስ የልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ዕቅድ ማስፈጸሚያ የሚሆን የቦታ ፈቃድ በክላርክ ካውንቲ ተሰጠ።
የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሃንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም በካሊፎርኒያ ምሥረታ
የኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሃንስ ወቅድስት አርሴማ አንድነት ገዳም በካሊፎርኒያ ምሥረታ አስመልክቶ በብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተላለፈ መልዕክት
ደብረ ምሕረት ቅ/ሚካኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ላስ ቬጋስ
ብጹእ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር የሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በአዲስ መልክ በኢትየኦጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሥነ ሕንጻ ዲዛይን ለሚገነባው የላስ ቬጋስ ደብረ ምሕረት ቅ/ሚካኤል ቤ/ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ አኖሩ።
መካነ ስብሃት ቅ/ሥላሴ የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሳክራሜንቶ
መካነ ስብሃት ቅ/ሥላሴ የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን በሳክራሜንቶ የአገልግሎት ሕንጻ ቤ/ክርስቲያን ግዢ ተጠናቆ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ደብረ ብሥራት ቅ/ገብርኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ፊኒክስ
ደብረ ብሥራት ቅ/ገብርኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን በፊኒክስ የአገልግሎት ሕንጻ ቤ/ክርስቲያን ግዢ ተጠናቆበሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅ/ዮሃንስ የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ አንድነት ገዳም
ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅ/ዮሃንስ ወቅ/ት አርሴማ የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ አንድነት ገዳም የ3700 ኤከር ቦታ ግዢ ተጠናቆ በብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅ/ዮሃንስ የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ አንድነት ገዳም
ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅ/ዮሃንስ ወቅ/ት አርሴማ የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ አንድነት ገዳም የ74 ኤከር መሬት ቦታ ግዢ ተጠናቆ በብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ደብረ ብሥራት ቅ/ገብርኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ላስ ቬጋስ
ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን በላስ ቬጋስ የሕንጻ ግንባታ ተጠናቆ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር እና በብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ደብረ ምሕረት ቅ/ሚካኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ኦክላንድ
ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን በኦክላንድ የአገልግሎት ሕንጻ ቤ/ክርስቲያን ግዢ ተጠናቆ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ዶ/ር ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
ደብረ ሰላም ቅ/ሚካኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ሳክራሜንቶ
ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል የኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን በሳክራሜንቶ የአገልግሎት ሕንጻ ቤ/ክርስቲያን ግዢ ተጠናቆ በብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።









