top of page
ሰሜን ካሊፎርኒያ ኔቫዳ እና አሪዞና ሀገረ ስብከት | EOTC N. CaNvAz Diocese

ጥምቀት
የምሥጢረ ጥምቀት መሥራች ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥምቀትን የመሠረተው በሦስት መንገድ ነው፦
-
በተግባር ራሱ ተጠምቆ እንድንጠመቅ አስተምሮናል፤ አርአያም ሆኖናል (ማቴ 3፡13)፡፡
-
በትምህርቱ “ያመነ የተጠመቀ ይድናል” (ማር 16፡16) እንዲሁም “እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔር መንግሥት ሊያይ አይችልም” (ዮሐ 3፡3-6) በማለት ጥምቀት ለድኅነት አስፈላጊ መሆኑን አስተምሯል፡፡
-
ለቅዱሳን ሐዋርያት በሰጣቸው ትዕዛዝ “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” (ማቴ 28፡19-20) በማለት ምስጢረ ጥምቀትን መስርቶልናል። ይህንንም መሠረት በማድረግ ሃይማኖታቸው የቀና ቅዱሳን አባቶች “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኀጢአት፣ ኀጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን” በማለት መሠረተ እምነትን ደንግገዋል፡፡
ስለሆነም በሀገረ ስብከታችን ያሉ አድባራት እና ገዳማት በ 40 እና በ80 ቀን በአጥቢያቸው የተጠመቁ ህጻናትን እንዲሁም ከኢ-አማኒነት ወደ አማኒነት ተመልሰው በአጥቢያቸው የተጠመቁትን ለሀገረ ስብከቱ በዚህ ድረ-ገጽ ሪፖርት እንዲያደርጉ የተዘጋጀ ሲሆን አሃዙ ለኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን ጠቅላይ ቤ/ክህነት በዓመቱ መጨረሻ ከሀገረ ስብከቱ በሪፖርት መልክ የሚቀርብ ይሆናል።
በሀገረ ስብከቱ አድባራት እና ገዳማት ጥምቀተ ክርስትና ያገኙ አማንያን ማሳወቂያ ፎርም
“ያመነ የተጠመቀ ይድናል” (ማር 16፡16)
“እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም” (ዮሐ 3፡3-6)
bottom of page